የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የታክስ ዕዳ አለባቸው ባላቸው 62 ግብር ከፋዮች ላይ ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ ስለጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ የተቋሙ የኮምዩኒኬሽንስ ዲሬክተር አቶ ሰውነት አየለ፣ ከጉዞ እግዱ በተጨማሪ ቢሮው ሌሎች አስተዳደራዊ ርምጃዎችንም እየወሰደ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በእግዱ ዙርያ አስተያየት የሰጡን አንድ የሕግ ባለሞያ ደግሞ፣ ቢሮው ይህን የማድረግ ሥልጣን በዐዋጅ እንደተሰጠው ገልጸው፣ ነገር ግን የዚህ ዐይነት ውሳኔ የሚተላለፈው፣ ታክስ ከፋዩ ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ይችላል የሚል በቂ ምክንያት ሲኖር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም