አዲስ አበባ —
በምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮቹ የጋራ ልማት ባለሥልጣን - ኢጋድ አማካኝነት በሚካሄደው ድርድር ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡት ሰባት ከእሥር የተፈቱ የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተቀሩት አራት እሥረኞችም እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ።
በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል መግለጫ የሰጡት ሰባቱ ሰዎች እስካለፈው ታኅሣስ አጋማሽ ድረስ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የነበሩ ናቸው፡፡
የፍትህ ሚኒስትር፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የቴሌኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር እና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡
የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ አድርጋችኋል በሚል ካለፈው ታኅሣስ 7/2006 ዓ.ም ጀምሮ በእሥር ላይ ቆይተው በምሥራቅ አፍሪካው በይነ-መንግሥታዊ የልማት ባለሥልጣን አማካይነት የተካሄደውን ድርድር ተከትሎ ከእሥር የተፈቱት በቅርቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ናይሮቢ ላይ ጥቂት ቆይታ አድርገው ትናንት፤ የካቲት 5/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የቀድሞዎቹ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት በዛሬው መግለጫቸው የአራቱ ታሣሪዎች መፈታት “በቀጣይነት ለሚካሄደው ድርድር ቁልፍ ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡
በድርድሮቹ ውስጥም ከእንግዲህ የሚሣተፉት እንደ ሦስተኛ ወገን እራሣቸውን ችለው መሆኑንም ተናግረዋል።
የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡