በከተሞች የሚታየውን የመኖርያ ቤት እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የመሬት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ የከተማ ዕቅድ ባለሞያው እና የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አርክቴክት ዮሐንስ መኰንን ገለጹ፡፡
የዐዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የጋራ መኖርያ ቤት ዕጦት እና የተጋነነ ኪራይ እየፈተናቸው እንደኾነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ፣ የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ ለማካተት ያደረገው ጥረት ባይሳካም፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ዐዲስ አማራጮችን እየተገበረ እንደኾነ፣ ከንቲባዋ ከዚኽ ቀደም አስታውቀው ነበር፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም