አዲስ አበባ —
ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለውና 29 ቢሊዮን ብር ወጭ የሚደረግበት የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ የከተማዋን ገፅታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር የተገለፀው ፕሮጀክት ይፋ እንደሚያደርጉ የተጠበቁት ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ግን በሥነ ስርዓቱ ላይ አልተገኙም፡፡
እሳቸውን በመወከል ጭምር ፕሮጀክቱን ያስጀመሩት፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ጠ/ሚኒስትሩ ያልተገኙት በአስቸኳይ ሥራ ስለተያዙ ነው ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ