በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የከተማ አስተዳደሩ የሰባት ተቋማትን አገልግሎቶች ለግሉ ዘርፍ ሊያስተላልፍ ነው


የከተማ አስተዳደሩ የሰባት ተቋማትን አገልግሎቶች ለግሉ ዘርፍ ሊያስተላልፍ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:26 0:00

የከተማ አስተዳደሩ የሰባት ተቋማትን አገልግሎቶች ለግሉ ዘርፍ ሊያስተላልፍ ነው

የዐዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በሰባት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ 24 አገልግሎቶችን፣ ለግሉ ዘርፍ በውክልና ለማስተላለፍ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከውሳኔው ላይ የደረሰው፣ የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እንደኾነ፣ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የድጋፍ እና ክትትል ዘርፍ ሐላፊ ዶር. ጣሰው ገብሬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በዚኽም፣ መንግሥት፣ በየመሥሪያ ቤቶቹ ውስጥ ያለውን ብልሹ አሠራር ለማስወገድ እንደሚሻ ሐላፊው ገልጸው፣ የመንግሥትን ወጪም እንደሚቀንስ አስገንዝበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን ያጋሩት፣ የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶር. ጫላ አምቢሳ ደግሞ፣ የመንግሥት አገልግሎትን ለግሉ ዘርፍ በውክልና መስጠት፣ በኢትዮጵያ እየተለመደ የመጣ አሠራር እንደኾነ አንሥተዋል፡፡ “ሒደቱ ግን ጥንቃቄ ይፈልጋል፤” ብለዋል፡፡ በውክልና በሚተላለፉት አገልግሎቶች ላይ፣ የግሉ ዘርፍ የተሻለ አሠራር እና ዐቅም ይኖረው እንደኾነ፣ መንግሥት በጥንቃቄ ማጣራት እንደሚገባው፣ መምህሩ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG