በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ተመለሱ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አሜሪካ ከነበራቸው ቆይታ ተመልሰው ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገልፀዋል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን ተናግረዋል። “... አሳፍረውኝ ተመለስሁ፤ ወደመጣሁበት ወደ አሜሪካ መለሱኝ” ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ብንደውልላቸውም ስልካቸው አልሠራም። በሌላ በኩል ከሚያገለግሉበት ተቋም ፍቃድ ስላለተሰጣቸው ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ለዋና ፀሐፊው ቅርበት እንዳላቸው የተናገሩ ሰው “አባ ጴጥሮስ አይሮፕላን ውስጥ በመሆናቸው ስልካቸው እንደማይሠራ፤ ነገር ግን ለመመለስ በተሣፈሩበት አይሮፕላን ውስጥ ሆነው እንዳነጋገሯቸው” ነግረውናል።

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄላን አብዲ ስልክ ላይ ደውለን አላገኘናቸውም።

በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከሣምንታት በፊት በሲኖዶስ ዕውቅና ወደ አሜሪካ ሄደው እንደነበር የመንበረ ፓትረያርክ ፅህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዛሬ በማኅበራዊ ገፁ ላይ አስፍሯል።

በቆይታቸውም ሐዋርያዊ አገልግሎት ማከናወናቸውን፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋራ ማክበራቸውንና ለአዳጊ ሕፃናት ማዕርገ ዲቁና መስጠታቸውን ገልጿል።

አቡነ ጴጥሮስ የቤተ ክርስትያኒቱ ከፍተኛ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚመለከተው የመንግሥት አካል ወደ ሀገር እንዲገቡ እንዲፈቅድላቸው ቤተክርስትያኒቱ ጥሪ ማቅረቧን መምሪያው በፌስቡክ ገፁ ላይ አስታውቆ ነበር።

ማብራሪያ እንዲሰጡን የደወልንላቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ መልሰው እንደሚደውሉልን ነግረን ይህ ዘገባ አየር ላይ እስከወጣ ሳይደውሉ ቀርተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG