የአስቸኳይ ጊዜ ኹኔታ ዐዋጁ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ከማብቃቱ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰሎሞን ገዛኽኝ ገለጹ፡፡
በተመሳሳይ፣ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋሉትን ፖለቲከኛ ዘለሌ ጸጋ ሥላሴን ጨምሮ አራት በእስር ላይ የሚገኙ “የእርስ በእርስ ጦርነት ይብቃ” በሚል መሪ ቃል ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎችም ለፍርድ እንዳልቀረቡ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ/ኢሕአፓ/ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ማብቃት ተከትሎ፣ እስረኞቹ ካልተለቀቁ አሊያም ለፍርድ ካልቀረቡ፣ በቀጣይ፥ “አካልን ነጻ የማውጣት ክስ እንመሠርታለን” ሲሉ፣ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም