በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መመሪያ ላይ የነዋሪዎችና የሕግ ባለሞያ አስተያየት


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

የጦር መሳሪያ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ መሳሪያቸውን በሁለት ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

የሕግ ባለሞያው አቶ ሞላልኝ መለሰ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት በሀገሪቱ ያለው የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው፣ ኅብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ በሚደረግበት ወቅት ከመሳሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወቅቱን ያገናዘበ ጥንቃቄ የሚደረግበት ሥርዓት ሊደረግ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ ለግሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች ሁሉ እንዲያስመዘግቡ እና በመሳሪያቸው አካባቢያቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ለጥበቃ መሰማራት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ የቅርባቸው ለሆነ ወይም ለሌላ የሚያምኑት ሰው በህጋዊ መንገድ አሳልፈው እንዲሰጡም የጠቆሙት ኃላፊው፣ የከተማው ነዋሪ አካባቢውን በመንደር ተደራጅቶ እንዲጠብቅም አሳስበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መመሪያ ላይ የነዋሪዎችና የሕግ ባለሞያ አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00


XS
SM
MD
LG