መንግሥት እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥርና ቅጣት ምክንያት፣ ነጋዴዎች ከትላንት ጀምሮ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ፣ አድማ ላይ መኾናቸውን የሱቅ ባለንብረቶች ተናግረዋል።
ከአድማው በተጨማሪ ከመጋዘን እቃ የማሸሽ ተግባርም መኖሩን የገለፁት ነጋዴዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ገበያ መቀዛቀዙን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፣ “ቁጥጥሩ የተጀመረው በርካታ ሕገ ወጥ አሠራሮች ስላሉ ነው” ሲሉ ዛሬ በተካሔደው የከተማው ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም