አዲስ አበባ —
ላለፉት ሰባት ዓመታት ካስተማርኩበት ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ “ፖለቲካዊ በሆነ ውሣኔ ተባርሬአለሁ” ሲሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ አስታውቀዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሣይንስ መምሪያ ወይም ሶሾል ሣይንስ ዲፓርትመንት የፍልስፍና መምህርና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው የቆዩት ዶ/ር ዳኛቸው የዩኒቨሲቲው አስተዳደር ኮንትራቴ እንዲታደስ ላቀረብኩት ይፋ ጥያቄ ይፋ ምላሽ አለመስጠቱም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡
ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መልስ ማግኘት አልተቻለም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡