በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሔራዊ ባንክ የብድር ጣሪያ ማሻሻያ ዐዲስ ባንኮችን እንደሚጎዳ ባለሞያዎች አመለከቱ


የብሔራዊ ባንክ የብድር ጣሪያ ማሻሻያ ዐዲስ ባንኮችን እንደሚጎዳ ባለሞያዎች አመለከቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00

የብሔራዊ ባንክ የብድር ጣሪያ ማሻሻያ ዐዲስ ባንኮችን እንደሚጎዳ ባለሞያዎች አመለከቱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ “የዋጋ ንረትን በመቀነስ ገበያውን ለማረጋጋት” በሚል መነሻ፣ ባሳለፍነው ዓመት መጫረሻ ላይ፣ ልዩ ልዩ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎች ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በዓመቱ ከተካሔዱት የፖሊሲ ማሻሻዎች አንዱ፣ በ2016 ዓ.ም. ባንኮች የሚሰጡት የብድር እድገት፣ በ14 በመቶ እንዲገደብ ማድረጉ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን ያጋሩ የፋይናንስ ባለሞያዎች፣ ርምጃው በዘርፉ ጥቅምም ጉዳትም እንደሚኖረውተናግረዋል፡፡የፋይናንስ ባለሞያው አቶ ይርጋ ተስፋዬ፣ የሀገር ውስጥ የብድር እድገትን መገደብ፣ በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውርለመቆጣጠር ቢያስችልም፣ ርምጃው ዐዲስ ባንኮችን ይጎዳል፤ ብለዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ የቡና ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉነህ አያሌው ደግሞ፣ ውሳኔው ተገቢ ቢኾንም፣ ገበያውን ለማረጋጋት ግን በቂ አይደለም፤ በማለት ይገልጻሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን የዋጋ ግሽበት መጠን ለማርገብ፣ ከንግድ ባንኮች ብድር ይልቅ፣ የመንግሥትን ብድር መገደብ የበለጠ ተጽእኖ እንደሚኖረው፣ አቶ ሙሉነህ ይናገራሉ፡፡

ባለሞያዎቹ፣ በሌሎቹም የብሔራዊ ባንክ ማሻሻዎች ላይም እይታቸውን ያጋሩን ሲኾን፣ በፋይናንስ ዘርፉ ያሉትን ዕድሎች እና ስጋቶችንም አትተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG