በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩና ቤታቸው እየፈረሰባቸው እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች፣ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት፣ መንግሥት ቃል ገብቶላቸው የነበረው የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ክፍያ እንዳልተፈፀመላቸው፣ ምትክ ቦታም እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው እየፈረሰ መኾኑን የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00

በወንዝ ዳር ልማት ምክንያት፣ ቤታቸው እየፈረሰ እንደሚገኝ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ወደየ ዘመዶቻቸው እንዲጠጉ አሊያም ተከራይተው እንዲኖሩ መፍትሔ ከጠየቋቸው ኃላፊዎች እንደተነገራቸው ተናግረዋል።

“ከተማችን እንድትቀየር እንፈልጋለን፣ ልማቱንም እንደግፋለን” በማለት የተናገሩት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ኾኖም መንግሥት ቅድሚያ ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው፣ ጊዜም እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ስለ ጉዳዩ ምላሽ የሰጠው ክፍለ ከተማው በበኩሉ፣ ለልማት ተነሺዎቹ ምትክ ቦታ መስጠቱን እና የካሳ ክፍያ ለመፈፀምም እየሠራ መኾኑን ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG