በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ እና የሀዋሳ ሰልፍ

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት መጠናቀቅን በመደገፍና መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሓት ቡድን ከፍቶታል ያሉትን ጥቃት ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። ነዋሪዎቹ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የህወሓትን አድራጎቶች እያየ ዝምታን መርጧል ሲሉም ከስሰዋል።
በሌላም በኩል የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት በተባለው ጊዜ መጠናቀቁን የሚደግፍና “አሸባሪ” ያሉትን “የህወሓት ቡድንና ጥቃቱን” የሚያወግዝ ሰልፍ ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች እና ከሃዋሳ ከተማ የተሰባሰቡ ነዋሪዎች በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ አድርገዋል።
የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የክልሉ ህዝብና መንግሥት ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩም የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናግረዋል።

ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG