በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለወራት ደብዛቸው የጠፋው የምክር ቤቱ አባል ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገለጸ


የኢትዮጵያ ፓርላማ
የኢትዮጵያ ፓርላማ
ለወራት ደብዛቸው የጠፋው የምክር ቤቱ አባል ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:21 0:00

ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ተይዘውና ደብዛቸው ጠፍቶ እንደቆየ የተገለጸው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የዐማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ሀብታሙ በላይነህ፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ረፋድ ወደ ቤታቸው ገብተዋል፤ ሲሉ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም፣ የምክር ቤት ተመራጩ እና የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ሀብታሙ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ መቀላቀላቸውን አረጋግጧል፡፡:

ይኹን እንጂ፣ ቤተሰቦቻቸውም ኾኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ አቶ ሀብታሙ በማንና የት ተይዘው እንደቆዩ መረጃው እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ፣አቶ ሀብታሙ በላይነህ ደብዛቸው ጠፍቶ የቆዩበትን ሁኔታና ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንም ከራሳቸው አንደበት ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ።

ከአማራ ክልል ምክር ቤትና ከፌደራል ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም እንደዚሁ አልተሳካም።

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ፓርቲን በመወከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የኾኑት አበባው ደሳለው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ሰዎችን የማገትና አስድዶ የመሰወር ድርጊት እንደሚያሳስባቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG