በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ ከታሰሩት አምስት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁለቱ ተፈቱ


በአዲስ አበባ ከታሰሩት አምስት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁለቱ ተፈቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

በአዲስ አበባ ከታሰሩት አምስት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁለቱ ተፈቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ትላንት በፖሊስ ተይዘው እንደታሰሩ ከገለጸቻቸው አምስት አገልጋዮቿ ውስጥ ሁለቱ፣ ዛሬ ዐርብ መፈታታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ፡፡

በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሚዲያ እና ኅትመት ዋና ክፍል ኃላፊ መምህር ዶር. አካለ ወልድ ተሰማ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ አገልጋዮቹ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን ማረጋገጣቸውን፤ ተናግረዋል። የተያዙበት ጉዳይ ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጡት አገልግሎት ጋራ የተያያዘ መኾን አለመኾኑን ለማጣራትም ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ትላንት ከተያዙት አገልጋዮች መካከል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ እንደሚገኙባቸው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG