በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ እንዲያፀድቀው ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአዲስ አበባ በተካሔደው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው” የተናገሩት የካፍ ፕሬዝደንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፣ የኢትዮጵያ ጥያቄ በካፍ አሠራር መሰረት ታይቶ ምላሽ እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በመጪው 2029 ዓ.ም. የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት 13 አገራት መጠየቃቸውንም አስታውቀዋል።

የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ እኢንፋንቲኖ በበኩላቸው፣ በፊፋ የዓለም ዋንጫ የሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ቁጥር ከቀጣዩ ውድድር ጀምሮ በእጥፍ እንደሚጨምር፣ በአዲስ አበባው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡

/ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG