ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር፣ በዐማራ ክልል ላይና እንዳስፈላጊነቱም በመላ ኢትዮጵያ ተፈጻሚ እንዲኾን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወጥቶ ለተጨማሪ ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ ዛሬ ረቡዕ የሚያበቃ ሲኾን፣ ከዐዋጁ ጋራ ተያይዞ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን/ኢሰመኮ/ ጠይቋል፡፡
በሌላ በኩል፣ ዐዋጁ በሚያበቃበት በዛሬው ቀን፣ ከ112 በላይ ሰዎች በሽብር ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
ተከሳሾቹ፣ ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ጋራ በተገናኘ በአዋሽ አርባ እና በአዲስ አበባ ታስረው የቆዩ መኾናቸውን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡
ካለፈው ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የዐሥር ወራት የኀይል ጊዜ የነበረው ዐዋጁ፣ ዛሬ የመጨረሻ ቀኑ ቢኾንም፣ በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡
መድረክ / ፎረም