በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ተሸኙ


የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ" በሚል መርህ ቃል ዛሬ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የሽኝት መረሃ ግብር ተደርጎላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ" በሚል መርህ ቃል ዛሬ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የሽኝት መረሃ ግብር ተደርጎላቸዋል።

ከሦስት ሺህ በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ" በሚል መርህ ቃል ዛሬ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የሽኝት መረሃ ግብር ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀናኣ ያደታ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሲናገሩ "ዘማቾች ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው ይመለሳሉ” ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ ሽኝት የተደረገላቸው በአባት አርበኞች ፣በከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና በነዋሪዎች ነው።

ከነዋሪዎች እና ባለሀብቶች የተሰበሰበ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ መደረጉን የገለጹት የከተማዋ ምክትል ከንትባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ድጋፉን ለመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀናአ ያደታ አስረክበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ተሸኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00


XS
SM
MD
LG