ዋሺንግተን ዲሲ —
በመሆኑም ታኅሣስ አሥር ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓመተ ምኅረት ማረፏን ማርዳት እንጂ ‘በዚህ ቀንና ዓመት ተወለደች’ ብሎ የሚናገር አልተገኘም፡፡ ለነገሩ ቆሞ የሚገኝ እማኝ ለመኖሩም እኮ እርግጠኞች አይደለንም፡፡
ዣ ዣ ጋቦር ትውልዶችን ዘልቃ የኖረችና የትውልዶችም መነጋገሪያ የነበረች አሜሪካዊት የፊልሞች ተዋናዪት፣ የቴሌቪዥን ዝግጅቶች ኮከብ ነበረች፡፡
የጋቦር መሠረተ-ዝርያ የአውሮፓዪቱ ሃንጋሪ ነች፡፡ የዋና ከተማዪቱ ቡዳፔሽት ተወላጅ ነች፡፡
ጋቦር ስምንት ባሎችን አግብታ የፈታች ብትሆንም ከዘጠነኛውና የመጨረሸው ባለቤቷ ላለፉት ሠላሣ ዓመታት አብራ ኖራለች፡፡
ዣ ዣ ጋቦር ካገባቻቸው ሚሊየነሮች መካከል ተዋናዩ ጆርጅ ሳንደርስ፣ ባለሆቴሉ የናጠጡ ከበርቴ ኮንራድ ሂልተን የሚገኙበት ሲሆን ሌሎችም ባለሚሊዮን ዶላር ነጋዴዎችና ዲፕሎማቶችም የዣ ዣን ሕይወት ጎራ እያሉ ጎብኝተዋል፤ እያቆራረጡም አልፈዋል፡፡
ጋቦር ከሚስተር ሂልተን የወለደቻት ብቸኛ ልጇ ፍራንቼስካ ሂልተን አምና ሞተች፡፡
ዣ ዣ እንዲያውም ይበልጥ የምትታወቀው ስለባሎቿና ስለፍቅር ሕይወት አብዝታ በመናገሯ ነውም ይባላል፡፡