በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘንድሮው የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊዎች ታውቀዋል


ኤልስ ቢያሊያትስኪ በእአአ 1980ዎቹ አጋማሽ ላይ በቤላሩስ የዲሞክራሲ እንቅስቃሴዎችን ከጀመሩት አንዱ
ኤልስ ቢያሊያትስኪ በእአአ 1980ዎቹ አጋማሽ ላይ በቤላሩስ የዲሞክራሲ እንቅስቃሴዎችን ከጀመሩት አንዱ

የዘንድሮው የኖቤል ሽልማት ለሦስት ተከፋፍሏል - በቤላሩስ ለሚገኝ አንድ የዲሞክራሲ አቀንቃኝና፣ በዩክሬንና በሩሲያ ለሚገኙ ሁለት የሰብዓዊ መብት ቡድኖች።

ኤልስ ቢያሊያትስኪ በእአአ 1980ዎቹ አጋማሽ ላይ በቤላሩስ የዲሞክራሲ እንቅስቃሴዎችን ከጀመሩት አንዱ ሲሆኑ፣ ሁለቱ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ደግሞ፣ “መሞሪያል” ወይም “መታሰቢያ” የተሰኘ የሩሲያ ተቋምና በዩክሬን የሚገኝ “የሲቪል ነፃነት ማዕከል” የተባለ ቡድን ናቸው።

ሽልማቱ ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማትና፣ ከ18 ካራት ወርቅ የተሰራ ሜዳሊያን ይጨምራል።

ባለፈው ዓመት የፊሊፒኗ ማሪያ ሮዛ እና የሩሲያው ዲሚትሪ ሙራቶቭ አሸናፊዎች ነበሩ። የዲሞክራሲና የዘላቂ ሠላም ቅድመ ሁኔታ የሆነውን የመናገር ነፃነት እንዳይደፈር በመጣራቸው ሽልማቱ እንደተሰጣቸው የኖቤል ኮሚቴው አስታውቋል።

ሙራቶቭ የወርቅ ሜዳሊያውን በዩክሬን በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ህፃናት እንዲውል ሸጧል።

እንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ በጎ አድራጊ በ103.5 ሚሊዮን ዶላር ገዝተውታል።

ከቀድሞ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች ውስጥ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ቀይ መስቀል፣ ኔልሰን ማንዴላ እና ባራክ ኦባማ ይገኙበታል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሠላምም ጦርነትም ያልነበረበትን 20 ዓመት ወደ ሠላማዊ ግንኙነት እንዲቀየር አስተዋጽኦ በማድረጋቸው በእአአ ጥቅምት 2019 የኖቤል ሽልማት መውሰዳቸው ይታወሳል።

በዓመቱ በሰሜን ኢትዮጵያ በፈነዳው ጦርነት ምክንያት ግን፣ “ሽልማቱ አይገባቸውም” እንዲሁም፣ “ሽልማቱን ይመልሱ” የሚሉ ነቀፌታዎችና ዘመቻዎች ተስተውለዋል።

XS
SM
MD
LG