“የአክሰስ ሪል ኢስቴት” ቤት ገዢዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቤታቸዉን ወይም ገንዘባቸውን የሚያገኙበትን እቅድ ማዉጣቱን የኢትዮጵያ መንግስት ያቋቋመው አንድ ኮሚቴ አስታወቀ።
ከ2005 ዓም አንስቶ ቤታቸዉን መረከብ የነረባቸውና ይህ ባለመሆኑ ቅሬታ ሲያቀርቡ የነበሩ ወደ 2000 የሚጠጉ ቤት ገዢዎች ጥያቄ በዚህ እቅድ ምላሽ ያገኛል፤ የሚል ተስፋ ተሰጥቷል።
“የአክሰስ ሪል ኢስቴት” በሚል መጠሪያ በሚታወቀው በዚህ የቤቶች ሻጭ ድርጅት የተከሰተውን ይህን ሁኔታ መነሻ በማድረግ መንግስት በአጠቃላይ በዘርፉ “አለ” ያለዉን ችግር ለመፍታት እንደሚሰራ የንግድ ሚኒስቴር አማካሪና መንግስት ያቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስታውቀዋል።