የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ ነገ ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ጋራ እንደሚወያዩ ከሶማሊያ ከመንግሥት ምንጮች መረጃውን ማግኘቱን ኤኤፍፒ አመልክቷል።
ሁለቱ ሀገራት የሻከረውን ግንኙነታቸውን ለማደስ በመሞከር ላይ ባሉበት ወቅት የሚካሄደው ጉብኝት “በአንካራ የተፈጸመውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግና ለማጠናቀቅ ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ እንደሆነ” ዘገባው አመልክቷል።
“በጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የባለሥልጣኖች ቡድን ነገ ሞቃዲሹ እንደሚደርስ ይጠበቃል” ሲሉ ለፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥቱ ቅርብ የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጭ መናገራቸውን ኤኤፍፒ በዘገባው አመልቷልክ።
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራስ ገዝ ከሆነችው ሶማሊላንድ ጋራ ባለፈው ዓመት የባሕር ዳርቻ በሊዝ ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሉ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት ሰፍኖ ነበር።
የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ ግን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት እንደሚመልሱ አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም