በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓብይ አህመድ ከፔንስ ጋር ተነጋገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን ዛሬ ማነጋገራቸውን ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣ መግለጫ አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን ዛሬ ማነጋገራቸውን ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣ መግለጫ አስታወቀ።
ዩናይትድ ስቴትስ ከአትዮጵያ ህዝብ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ምክትል ፕሬዚዳንቱ። በድጋሚ አረጋግጠው የሰብአዊ መብቶች አያያዝን፣ የንግዱን አካሄድ ማሻሻልና ከኤርትራ ጋር ሰላም መፍጠርን ጨምሮ "ታሪካዊ" ሲሉ የጠሩትን የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን የለውጥ ጥረት አድንቀዋል።

screen shot pm abiy with v pre mike pence
screen shot pm abiy with v pre mike pence

በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አካባቢያዊ ግጭቶችን ለማስወገድ ኢትዬጵያ ያላትን የመሪነት ቦታ እንድትቀጥል እንደሚያበረታቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ማስታወቃቸውን ዋይት ሃውስ በመግለጫው አስፍሯል።
እንዲሁም በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
ሁለቱ መሪዎች በሀገሮቻቸው መካከል ላሉ የጋራ እሴቶች ትኩረት ሰጥተው የተነጋገሩ ሲሆን በመጪ ጊዜያትም ይበልጥ የተጠናከረ አጋርነትን ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኛነት ማረጋገጣቸውን ይኸው የዋይት ሃውስ የምክትል ፕሬዚዳንቱ ቢሮ መግለጫ አመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG