በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአቢጃን ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሕይወት በመቅጠፍ ላይ ነው


የእሳት አደጋ ሰራተኛው በኮኮዲ አንግሬ በጎርፍ ውሃ በኩል ነዋሪውን እያሻገረ፣ አቡጃን፤ አይቮሪ ኮስት እአአ ሰኔ 14/2024
የእሳት አደጋ ሰራተኛው በኮኮዲ አንግሬ በጎርፍ ውሃ በኩል ነዋሪውን እያሻገረ፣ አቡጃን፤ አይቮሪ ኮስት እአአ ሰኔ 14/2024

በአይቮሪ ኮስት ትልቋ ከተማ አቢጃን በደረሰ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ቢያንስ 24 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

በአራት እጥፍ የከበደ ዝናብ የምዕራብ አፍሪካዊቱን ሃገር የኢኮኖሚ መዲና ሲመታ፣ ከፍተኛ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ተከስቷል።

ከወዲያኛው ሳምንት ሐሙስ እስካለፈው ቅዳሜ በጣለው ዝናብ ቢያንስ 24 ሰዎች እንደሞቱ የሲቪሎችን ደህንነት የሚከታተለው መንግስታዊ ቢሮ አስታውቋል።

በጎርፍ የተወሰዱ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።

ስድስት ሚሊዮን ነዋሪዎች ባሏት አቢጃን፣ አደገኛ ዝናብና ተከትሎ የሚመጣው ጎርፍ በተደጋጋሚ ይከሰታል። ድሆች ጎርፍ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች እንደነገሩ በተሰሩ መጠለያዎች ውስጥ መኖራቸው ለአደጋው ተጋላጭ አድርጓቸዋል።

ባለፈው ዓመት በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ 30 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG