በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እማሆይ ፀጋ አቢ አዲ ላይ በጎ እያደረጉ ነው


መቀሌ፦ መቀሌ
መቀሌ፦ መቀሌ

እማሆይ ፀጋ ግርማይ ትግራይ አቢ አዲ ውስጥ ተጠልለው ለሚገኙ 4400 ተፈናቃዮች ያገኙትን በማቃመስ እየረዱ መሆናቸውን እዚያው ተገኝቶ እርሳቸውንና ከተፈናቃዮቹ መካከል የተወሰኑትን ያነጋገረው የመቀሌ ሪፖርተራችን ዓለም ፍሰሃ ዘግቧል።

እማሆይ ምንኩስና ከተቀበሉ ሃያ ዓመታት ያሳለፉት እማሆይ ፀጋ ለቀናት እህል ያልቀመሱ ተፈናቃዮችን ማየታቸው ያለ የሌላቸውን የራሳቸውንም የልጃቸውንም ሸጠው ሰዉን ወደማቃመስ እንደገቡ ተናግረዋል።

እርዳታ ፈላጊው ብዙ መሆኑንና “አቅርቦት ግን የለም” የሚሉት እማሆይ አነስተኛ ቢሆንም ሰዉ ከያለበት እያገዛቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

እማሆይ ፀጋ አቢ አዲ ላይ በጎ እያደረጉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00


XS
SM
MD
LG