በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ግንኙነት ኃላፊው መታሰራቸውን ባይቶና ፓርቲ ገለፀ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

በድጋሚ የታደሰ ጹሁፍ፦

የትግራዩ ተቃዋሚ የባይቶና ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብሮም በርሄ መታሰራቸውን ፓርቲው ለቪኦኤ ገልጿል።

የባይቶና ፓርቲ የህግ ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ቀደም ሲል የፖሊስ አባላት የአቶ ክብሮምን ባለቤት ከቤታቸው ይዘው መውሰዳቸውንና አቶ ክብሮምን እንዲያቀርቡ እንደጠየቋቸው፤ በኋላም አቶ ክብሮም እጃቸውን ትናንት ‘ከምሽቱ አንድ ሰዓትና ሁለት ሰዓት ይሆናል’ ባሉት ጊዜ ለፖሊስ መስጠታቸውንና አሁን አቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አቶ ክብሮም የታሰሩትን ምክንያት ባይቶና ፓርቲ አልገለፀም። የአቶ ክብሮም ባለቤት በኋላ የተለቀቁ ቢሆንም በስልክ አግኝቶ ለማነጋገር ሪፖርተራችን ገብረሚካዔል ገብረመድኅን ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ አመልክቷል።

ስለ አቶ ክብሮም እሥራትና ለምን እንደተያዙ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቃል አቀባይ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን ገብረሚካዔል ጠይቆ መረጃ እንደሌላቸውና ጉዳዩን የሰሙትም ከእርሱ መሆኑን፣ አጣርተው መልስ እንደሚሰጡት መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG