በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከምክር ቤቱ አመጽ በኋላ አሜሪካውያን ስለዲሞክራሲያቸው ሰግተዋል


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ዙሪያ ላይ የሽቦ አጥር
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ዙሪያ ላይ የሽቦ አጥር

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ አንድ ዓመት በኋላ አሜሪካውያን በአገራቸው ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት በእጅጉ ያሳሰባቸው መሆኑን መግለፃቸው ተገለጠ፡፡

ትናንት እሁድ የወጡ ሁለት የህዝብ አስተያየት ድምጽ መሰብሰቢያ ተቋማት ይፋ ባደረጉት መረጃ እንደተመለከተው አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት አሜሪካውያን በመንግሥት ላይ የሚደረግ አመጽ አንዳንድ ጊዜ ምክንያታዊ ነው ብለዋል፡፡

በሲቢኤስ ቴሌቪዥን ዜና አውታር የተሰበሰበ ድምጽ እንዳለመለከተው አስተያየታቸውን ከሰጡት ውስጥ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት አሜሪካውያን እኤአ ጥር 6 በዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ የተደረገው ጥቃት “የፖለቲካ ጥቃት እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ብለው ማመናቸውንና የአሜሪካ ዴሞክራሲ አደጋ ላይ ነው ብለው እንደሚሰጉ” አስታውቀዋል፡፡

በሌላም በኩል አሜሪካውያን ስለ ዴሞክራሲያቸው የነበራው ኩራት የቀነሰ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ዴሞክራሲያቸውን አሰመልክቶ እኤአ በ2002፣ 90 ከመቶ የነበራቸው ኩራት ዛሬ ወደ 54 ከመቶ መውረዱን የዋሽንግተን ፖስት እና የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ከህዝቡ ባሰባቡት ጥናታዊ ቅኝት አመልክተዋል፡፡

እኤአ ጥር 6 በምክር ቤቱ የተቃጣው ጥቃትን አስመልክቶ ለሲቤኤስ ቴሊቭዥን አስተያየታቸው ከሰጡት መካከል፣ 28 ከመቶ የሚሆኑት፣ የምርጫውን ውጤት ለመጠበቅ ኃይል መጠቀም አሰፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዋሽንግተን ፖስት አስተያየታቸው ከሰጡት ደግሞ፣ 34 ከመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን፣ በመንግሥት ላይ የሚደረግ አመጽ አንዳንዴ አስፈላጊና ምክንያታዊም ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG