በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በጦርነቱ በተጎዱት የአፋር እና የአማራ ክልል አካባቢዎች አስከፊው የሰብዓዊ ረድዔት ችግር ቀጥሏል" ተመድ


ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች
ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በተጎዱት የአፋር እና የአማራ ክልሎች አካባቢዎች አሁንም እጅግ ከባድ የሆነው የሰብዓዊ ረድዔት ችግር እንደቀጠለ መሆኑን የተመድ ቃል አቀባይ ተናገሩ።

ስቴፋን ዱጃሪች ባለፈው ዐርብ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ገለጻ ባለፈው ህዳር የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደትግራይ ክልል ሰብዓዊ ረድዔት እየተላከ መሆኑን ገልጸዋል።

3 ሺህ የጭነት መኪናዎች 105 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እንዲሁም የጤና፣ የመጠለያ፣ የውሃ እና ሌሎችም አቅርቦቶች ማድረሳቸውን አብራርተዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ማጓጓዣ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደክልሉ መደበኛ በረራዎችን እያካሄዱ መሆኑም ዱጃሪች አክለው ገልጸዋል።

"ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ ቁጥራቸው ከሶስት ሚሊዮን ለሚበልጥ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ተሰጥቷል። ዕርግጥ ነው በሰሜኑ የድንበር አቅራቢያ ያሉ አንዳንድ አካባቢዎች እና ከመንገድ ራቅ ብለው ያሉትን ጨምሮ ለመድረስ አዳጋች የሆኑ አካባቢዎች አሉ።

በጦርነቱ በተጎዱት የአፋር እና የአማራ ክልል አካባቢዎች ያለው እጅግ ከባድ የሆነው የሰብዐዊ ረድዔት ችግር አሁንም እንደቀጠለ ነው" ብለዋል ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች።

አክለውም ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እየተመለሱ ባሉባቸው አካባቢዎችም ጭምር የምግብ እና ሌላም ዕርዳታ የማከፋፈሉ እንቅስቃሴ ክፍተትም ቢኖርም ቀጥሏል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአፍሪካ ቀንድን ባጠቃው ከባድ ድርቅ የምስራቅ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ማሕበረሰቦች አሁንም እየተጎዱ መሆናቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG