የሚልዋኪ ከተማ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን መኖሪያቸው ካደረጓቸው የማዕከላዊ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች መካከል አንዷ ናት።
ለእነዚህ ማኅበረሰቦች ትብብር እና ወንድማማችነት እየሠሩ ከሚገኙት መካከል የከተማው ብቸኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ለማሪያም ትገኝበታለች።
ከትውልድ ሀገራቸው ርቀው ለሚኖሩት ኢትዮጵያን እና ኤርትራዊያን በዋነኝነት መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመችው ቤተክርስቲያን፣ ከዚህ ተሻግራ ወጣቶች ስለ ባህል እና ማንነታቸው እንዲያውቁ ፣ በቀለም ትምህርት እንዲበረቱ የሚያግዙ መርሀ ግብሮችን ዘርግታለች።
መድረክ / ፎረም