በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ግጭት ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ተመድ ገለጸ


ፎቶ ፋይል - በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጠረ ግጭት ቀዮአቸውን ለቀው የሚሰደዱ
ፎቶ ፋይል - በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጠረ ግጭት ቀዮአቸውን ለቀው የሚሰደዱ

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጠረ ግጭት፣ 6ነጥብ9 ሚሊዮን ሰዎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው እንደተፈናቀሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ገልጿል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት፣ ከ26 የኮንጎ ግዛቶች የተገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ባወጣው ዘገባ፣ ለዐሥርት ዓመታት የዘለቀው ግጭት፣ ለነዋሪዎች መፈናቀል ቀዳሚው ምክንያት እንደኾነ ገልጿል።

ድርጅቱ በዘገባው፣ ቢያንስ 80 በመቶ የሚኾኑ ተፈናቃዮች፣ በምሥራቅ ኮንጎ ሰሜን ኪቩ፣ ደቡብ ኪቩ፣ ኢቱሪ እና ታንጋኒካ አውራጃዎች እንደሚኖሩ አስታውቋል፡፡

ከእነዚኽም በርካቶቹ፣ ከክልሉ ወርቅ እና ሌሎች ሀብቶች ድርሻ ለማግኘት በሚፈልጉ ታጣቂ ቡድኖች እንደሚመሩ፣ የስደተኞቹ ድርጅት ጠቁሟል፡፡

አንዳንዶቹ ታጣቂ ቡድኖች፣ በኮንጎ አጎራባች አገሮች ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲኾን፣ ሌሎቹም ማኅረሰባቸውን ለመከላከል እንደሚጥሩ፣ ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

የአካባቢው ቀውስ ከመረጋጋት ይልቅ እየተባባሰ በመምጣቱ፣ በአገሪቱ፣ ከሁለት ዐሥርት ዓመታት በላይ ሲሠራ የቆየው የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮም፣ ከኮንጎ ለቆ እንዲወጣ ግፊት ገጥሞታል።

በተለይ በዚኽ ወር፣ እያደገ በመጣው ጥቃት የተበሳጨው የኮንጎ መንግሥት፣ ምንም ዐይነት የተጨበጠ ነገር አልሠራም፤ ሲል የተቸውን፣ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ኃይል፣ እስከ ታኅሣሥ ወር ድረስ፣ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ መመሪያ ሰጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG