በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሩብ ቢሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይሻሉ


ፎቶ ፋይል - ተፈናቃዮች ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ ወደሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ሲደርሱ እአአ 09/21/2022
ፎቶ ፋይል - ተፈናቃዮች ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ ወደሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ሲደርሱ እአአ 09/21/2022

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት፣ በ58 ሀገራት የሚገኙና ከሩብ ቢሊዮን በላይ የሚኾኑ ሰዎች፥ በግጭት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአስከተለው መዘዝ፣ እንዲሁም በዩክሬን እየተካሔደ ባለው ጦርነት ሳቢያ፣ የከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ገጥሟቸው እንደነበር፣ አንድ ዐዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በአውሮፓ ኅብረት ትብብር በሚደገፈው፣ ዓለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት የተሰኘው የረድኤት ድርጅቶች ኅብረት ይፋ በኾነው ጥናት፣ የምግብ ዕጦቱ በሰባት አገሮች ሞት ማስከተሉ ተገልጿል፡፡ እነኚኽ ሰባት ሀገራት፥ ሶማሊያ፣ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሄይቲ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ ሱዳንና የመን እንደኾኑ ጥናቱ አስፍሯል፡፡

የምግብ ዋስትና ዕጦት የገጠማቸውና አስቸኳይ ርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር፣ 258 ሚሊዮን መድረሱን ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

XS
SM
MD
LG