በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ ከ350 በላይ ፍልሰተኞችን ከባሕር አስመለሰ

Migrants are detained at Abosetta base in Tripoli, Libya, May 10, 2017.
Migrants are detained at Abosetta base in Tripoli, Libya, May 10, 2017.

አንድ የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ትላንት ከ350 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ባህር ላይ አግኝቶ መልሶቸዋል። ከጀርመን የመድህን ጀልባ ጋር ሊጋጭ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን የደረሰ ጉዳት ካለ አልተገለፀም።

አንድ የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ትላንት ከ350 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ባህር ላይ አግኝቶ መልሶቸዋል። ከጀርመን የመድህን ጀልባ ጋር ሊጋጭ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን የደረሰ ጉዳት ካለ አልተገለፀም።

“ሳብራታ” ከተባለችው የጠረፍ ከተማ የተመለሱት ስደተኞች ወደ ትሪፖሊ ተወስደዋል። የሊብያ የባሕር ኃይል ቃል አቀባይ እንደሚለው ስደተኞቹ አንድ በእንጨት የተሠራ ጀልባ ላይ ተፋፍገው ነበር የተገኙት።

የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ወደነሱ ስትጠጋ አንድ የጀርመን የመድህን ጀልባ ደርሶ ከሊብያው መርከብ ጋር ሊጋጭ ተቃርቦ እንደነበር ቃል አቀባዩ ተናግሯል።

የባሕር ጥበቃ የተባለው የጀርመን የመድኅን ቡድን ፍልሠተኞቹን ወደ ሊብያ መመለሱ ለ”ደኅንነታቸው አደገኛ ነው” በሚል ሳይሆን አልቀረም ከሊብያው መርከብ ጋር የተፋጠጠው ተብሏል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG