የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ከዋሺንግተን ዲ ሲ በአማርኛ ቋንቋ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያና ኤርትራ አድማጮቹ የሚያስተላለፍፈው ፕሮግራም ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ እየታፈነ መሆኑን የመሐንዲስ ክፍላችን አረጋግጧል።
ችግሩን ለማስወገድ VOA በአምስት የተለያዩ ሞገዶች ሥርጭቱን የቀጠለ ቢሆንም፥ እናንተ ምናልባት ለመስማት ትቸገሩ ይሆናል ብለን እንሰጋለን።
ለማንኛውም በሥርጭታችን ላይ ጣልቃ እየገባ፥ ጥራቱን በማፈን ላይ የሚገኘውን የችግሩን ምንጭ ለመለየትና፥ ባስቸኳይ ለማረም ጥረት እያደረግን መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።
ለትዕግስታችሁ ከልብ እናመሰግናለን።