በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ተመራማሪ የታይም መጽሔት "የዓመቱ ግሩም ልጅ" ክብርን አገኘ


የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሔማን በቀለ
የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሔማን በቀለ

የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሔማን በቀለ፣ የታይም መጽሔት የዓመቱ ድንቅ ልጅ ወይንም ‘Kid of the Year’ ተብሎ ተመርጧል።

በአሜሪካ፣ ፌርፋክስ ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ ኗሪ የሆነው ሔማን የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያገለግል በአነስተኛ ዋጋ የሚገኝ ሳሙና ፈጣሪ ነው። የሔመን ግኝት በተለይ በድህነት ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቆዳ ካንሰር ህክምናን ተደራሽ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

የቆዳ ሕክምናን ዘርፍ የቀየረው “ምርጥ አዳጊ ሳይንቲስት” እና የግብረ ሠናይ ተቋም ምሥረታ ሕልሙ  
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00

ታይም መጽሔት ሔመንን የመረጠው ወደፊት ሜላኖማ የሚባለውን ጨምሮ የቆዳ ካንሰርን የሚያክም መድሃኒት በአዲስ እና የበለጠ ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማድረስ የሚያስችል ሳሙና በመስራቱ መሆኑን አስታውቋል።

ገና የ4 ዓመት ልጅ እያለ ከወላጆቹ ጋር ወደ አሜሪካ የመጣው ሔመን፣ ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ላይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሰዎች ሳሙናውን በቀላሉ ማግኘት ይችሉ ዘንድ ድርጅት ማቋቋም እንደሚፈልግ ተናግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG