በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቆዳ ሕክምናን ዘርፍ የቀየረው “ምርጥ አዳጊ ሳይንቲስት” እና የግብረ ሠናይ ተቋም ምሥረታ ሕልሙ  


የቆዳ ሕክምናን ዘርፍ የቀየረው “ምርጥ አዳጊ ሳይንቲስት” እና የግብረ ሠናይ ተቋም ምሥረታ ሕልሙ  
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00

ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ በቨርጂኒያ ግዛት የ“ደብሊው ቲ ውድሰን” ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የኾነው የ14 ዓመቱ ኢትዮ-አሜሪካዊ ሔማን በቀለ፣ የአሜሪካ ከፍተኛ የወጣት ሳይንቲስት 3ኤም ውድድር ላይ፣ የ“ምርጥ አዳጊ ሳይንቲስት ሽልማት”ን ተቀብሏል።  ሔማን፣ የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል፣ በቀላሉ ገበያ ላይ ሊቀርብ የሚችልና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ደረቅ ሳሙና ፈጥሯል። 

አዳጊው በዚኽ ፈጠራው፣ የ25ሺሕ ዶላር አሸናፊ ሲኾን፣ ገንዘቡን፥ ለከፍተኛ ትምህርት አሊያም ምርምሩን አስፋፍቶ ለማስኬድ እንደሚጠቀምበት፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

ይኸው የፈጠራ ሥራውም፣ ከቀጣይ ምርምሮች በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የመድኃኒት ጥራት እና ቁጥጥር ተቋም ማረጋገጫውን ሲያገኝ፣ በቆዳ ካንሰር ሕክምና ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል። በተለይም፣ አዳጊ ሀገራት እና በድህነት ውስጥ የሚገኙ ማኅበረሰቦች በቀላሉ እንዲያገኙት፣ ግብረ ሠናይ ተቋም የመመሥረት ሕልም እንዳለው ሔማን አስታውቋል።

ኤደን ገረመው፣ ሔማን በቀለንና ወላጆቹን አነጋግራ ያሰናዳቸው ዘገባ ይቀጥላል።

XS
SM
MD
LG