በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዙማ ከእስር መለቀቅ ሕጋዊ አይደለም ተባለ


የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ
የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ

የደቡብ አፍሪካ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ‘የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በጤና እክል የተነሳ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉ ሕገ-ወጥ ነው’ አለ።

እንደ እውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 ዓም ዙማ ችሎት በመዳፈር ወንጀል የተበየነባቸውን የ15 ወራት የእስር ጊዜያቸውን በጀመሩ ከስምንት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጋቸው ይታወቃል። ያም ብያኔ በስልጣን ላይ ባሉበት ወቅት የተካሄደውን የጸረ-ሙስና ምርመራ አስመልክቶ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን ለመስጠት ያለመፍቀዳቸውን የተከተለ ነበር።

በጤና መታወክ የተነሳ በሚል ለዙማ የተሰጠው የእስር እፎይታ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ወዳጅ በሆኑት የማረሚያ ቤቶች አገልግሎቱ አርተር ፍሬዠር ነው የተመራው። በአንጻሩ የትላንቱን የፍርድ ቤቱን ብይን የከትሎ ዙማ ወደ እስራቸው ይመለሱ እንደሁ ወዲያውኑ ግልፅ አልሆነም።

ካሁን ቀደም በዙማ እስር ሳቢያ በተቀሰቀሰ ሁከት ከ300 በላይ ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸው ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG