በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዚምባቡዌ - በኩፍኝ ሰማንያ ህፃናት ሞቱ


በሀገሪቱ ማኒካላንድ ግዛት ህፃናት የክፉኝ ክትባት ሲሰጡ
በሀገሪቱ ማኒካላንድ ግዛት ህፃናት የክፉኝ ክትባት ሲሰጡ

ዚምባቡዌ ውስጥ እየተስፋፋ ባለው የኩፍኝ ወረርሽኝ ምክንያት ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ ሰማንያ ህፃናት መሞታቸውን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ወረርሽኙ የተቀሰቀሰው ባለፈው ሚያዝያ መጀመሪያ በአንድ የቤተ ክርስትያን ውስጥ ከተካሄደ ክብረ በዓል በኋላ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ወረርሽኙ በመላ ሀገሪቱ መዛመቱን የጤና ሚኒስትሩ ጃስፐር ቺሜድዛ ማረጋገጣቸውንና ለቫይረሱ የተጋለጡ 125 ሰዎች በምርመራ መገኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ከሞቱት ህፃናት የሚበዙት ከዕምነታቸው ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የክትባት ተጠቃሚ ያልሆኑ ማኅበረሰቦች አባላት መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG