በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይኤምኤፍ ለዛምቢያ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ፈቀደ


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) የፋይናንስ ቀውስ የገጠማት ዛምቢያን ለመታደግ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ብድር መፍቀዱን ትላንት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሃኬንዴ ሂችሌማ ደግሞ የአገሪቱን ፋይናንስና የመበደር አቅም ለማሻሻል በዛሬው እለት ቃል መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

ከተፈቀደው የተራዘመ የብድር መርኃ ግብር ውስጥ በእዳ ለተዘፈቀቸው ዛምቢያ ወደ 185 ሚሊዮን ዶላር በአስቸኳይ እንደሚለቀቅ አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በኢኮኖሚ አመራርና አያያዝ ጉድለት እንዲሁም ኮቪድ 19 ወረረሽኝ ዘመን እዳዋን መክፈል አለመቻሏን በመግለጽ ዛምቢያ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ አገር መሆንዋም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ከአገሪቱ ጠቅላላ ምርት ውስጥ ከ120 ከመቶ በላይ በእዳ ተይዞ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የአገሪቱን እዳ መልሶ ለማዋቀር ወሳኝ እምርጃ ነው ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG