በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሁለት ባለስቲክ ሚሳዬሎችን መትታ መጣሏን አስታወቀች


ፎቶ ፋይል፦ የየመን ሁቲ አማጽያን በአቡዳቢ የሚገኘውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ በመምታት ሦስት ሰዎችን በመግደል ሌሎች ስድስት ሰዎችን ደግሞ ማቁሰላቸው መዘግቡ ይታወሳል።
ፎቶ ፋይል፦ የየመን ሁቲ አማጽያን በአቡዳቢ የሚገኘውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ በመምታት ሦስት ሰዎችን በመግደል ሌሎች ስድስት ሰዎችን ደግሞ ማቁሰላቸው መዘግቡ ይታወሳል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ አቡዳቢ ኢላማ ያደረጉ ሁለት የባለስቲክ ሚሳዬል ጥቃቶችን ዛሬ ሰኞ መትታ ማምከኗን አስታወቀች፡፡

የኤምሬቱ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተመተው የወዳደቁትየሚሳዬሎቹ ቁርጥራጮች በሰው ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሳቸው ተገልጿል፡፡

መግለጫው አክሎ እንዳስታወቀው

“የተባበሩት አረብ ኤምሬት የትኛውንም ጥቃት በመመከት አገሪቱን ከሁሉም ጥቃቶች ለመከላከል አስፈላጊውን እምርጃ ሁሉ ትወስዳለች” ብሏል፡፡

ባላፈው ሳምነት የየመን ሁቲ አማጽያን በአቡዳቢ የሚገኘውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ በመምታት ሦስት ሰዎችን በመግደል ሌሎች ስድስት ሰዎችን ደግሞ ማቁሰላቸው መዘግቡ ይታወሳል፡፡

የተባበሩት ኤምሬት በሳኡዲ አረቢያ ከሚመራውና በየመን ክሁቲዎች ጋር እየተዋጋ ከሚገኘው የትብብር ጦር አንዷመሆኑም ይታወቃል፡፡

ሳኡዲ መንግሥትም ባለፈው እሁድ ከሁቲዎች የተተኮሰ የባለስቲክ ሚሳዬል፣ በደቡብ ሳኡዲ አረብያ ውስጥ መውደቁንና አንድ ሰው ማቁሰሉን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG