በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን ሁቲ አማጽያን ልጆችን በተዋጊነት ላለማሰለፍ መስማማታቸውን የተመድ ገለጸ

ፎቶ ፋይል - የ12 ዓመት ታዳጊው ካህላን በየመን የሁቲ አማፂያን የቀድሞ ወታደር ሲሆን የመን ከቤተሰቦቹ ጋር በተጠለለበት የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የጦር መሳሪያ እንዴት እንደሚጠቀም ሲያሳይ፣ በማሪብ፣ የመን እአአ ሀምሌ 27/2018
ፎቶ ፋይል - የ12 ዓመት ታዳጊው ካህላን በየመን የሁቲ አማፂያን የቀድሞ ወታደር ሲሆን የመን ከቤተሰቦቹ ጋር በተጠለለበት የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የጦር መሳሪያ እንዴት እንደሚጠቀም ሲያሳይ፣ በማሪብ፣ የመን እአአ ሀምሌ 27/2018

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀው የየመን ሁቲ አማጽያን ልጆችን በውጊያ ላለማሰማራት መስማማታቸውን ገልጿል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ እንደገለጹት አማጽያኑ ልጆችን በውጊያ እንዳያሰማሩ፣ እንዳይመለምሉ እና በህጻናትን እንዳይገድሉ እንድሁም ትምህርት ቤቶችን እና ሆስፒታሎችን እንዳያጠቁ የተዘጋጀ የድርጊት መርሃ ግብር ፈርመዋል።

አማጽያኑ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በሰራዊቱ ውስጥ ያሉ ልጆችን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ነው የድርጅቱ ቃል አቀባይ ያመለከቱት።

ሰባት ዓመታት ባስቆጠረው የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት በሺሕዎች የተቆጠሩ ልጆች ተዋግተዋል። የተባለውን የድርጊት ዕቅድ ሁቲዎቹ የልጆችን ደህንነት ለመጠበቅ ተብሎ የተዘጋጀ ሲሉ ገልጸውታል።

የተመድ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚታወቀው የየመን መንግሥትም እአአ በ2014 ዓም ተመሳሳይ ሰነድ እንደፈረመ የተመድ አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG