በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ ከመቶ በላይ የየመን እስረኞችን ልትለቅ ነው


ሳዑዲ አረቢያ ከመቶ በላይ እስረኞችን ዛሬ ልትለቅ እንደምትችል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡

ውሳኔው በቅርቡ የተደረገውና በየመን ተፋላሚ ወገኖች መካከል 900 የሚሆኑ እስረኞች ልውውጥ የተደረገበት ሂደት አካል አለመሆኑ ታውቋል፡፡

የእስረኞች ልውውጡ የመጣው ሳዑዲ አረቢያና ኢራን ግንኙነታቸውን ወደ ነበረበት ለመምለስ በተስማሙ በወሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ በየመን የሚገኘውንና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን መንግሥት ስትደግፍ፣ ኢራን ደግሞ የሁቲ አማጺያንን ትደግፋለች፡፡

በየመን እየተካሄደ ያለው ግጭት ወትሮውንም ከባድ የነበረውን የሰብዓዊ ሁኔታ ማባባሱ ሲነገር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ደግሞ ከየመን ሕዝብ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው ሰብዓዊ ድጋፍና ከለላ ይሻል፡፡

XS
SM
MD
LG