በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ወደ ጦርነት እንዳትመለስ ሥጋት ሰፍኗል


ልዩ ልዑኩ ሃንስ ግሩንድበርግ
ልዩ ልዑኩ ሃንስ ግሩንድበርግ

በየመን የተካሄደው ተኩስ ማቆም የግዜ ገደቡ ባበቃበት በዚህ ወቅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ የስድስት ወሩን ተኩስ ማቆም እንደገና ለማንሰራራት እየተሯሯጡ ነው።

የግዜ ገደቡ በማለቁ ጦርነት እንደገና እንዳያገረሽ ሲሰጋ፣ የሁቲ አማጺያኑ በሳዑዲ አረቢያና በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላይ ያሚያሠሙትን ዛቻ አባብሰዋል።

ልዩ ልዑኩ ሃንስ ግሩንድበርግ የተኩስ ማቆሙን እንደገና ለመተግበር የማያቋርጥ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት አማጺያን እና በሳዑዲ ከሚመራው የመንግሥት ደጋፊ ኃይል ጋር ላለፉት 7 ዓመታት ወጊያ ላይ ከርመው የነበረ ሲሆን፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ፣ እንደ ተመድ ከሆነ ደግሞ በዓለም አስከፊውን የሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል።

ያህያ ሳሪ የተባሉ የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ትናንት እሁድ በሳዑዲና በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላሉ ነዳጅ ኩባንያዎች በትዊተር ማስጠንቀቂያ ልከዋል። “ሁኔታቸውን አስተካክለው ለቀው እንዲወጡ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል ቃል አቀባዩ።

XS
SM
MD
LG