በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ባይደን የሳምንቱ የአገር ውስጥ አጀንዳቸውን እያስተዋወቁ ነው


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ ጋር በመሆን ባላፈው ሳምንት ከዴሞክራቶች ጋር ተወያይተዋል
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ ጋር በመሆን ባላፈው ሳምንት ከዴሞክራቶች ጋር ተወያይተዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዚህ ሳምንት የአገር ውስጥ አጀንዳዎቻቸውን ለማስተዋወቅ እቅድ ይዘዋል፡፡

የ1.2 ትሪሊዮን ዶላር መሠረት ልማት የበጀት እቅዳቸውንና የ 3.5 ትሪሊዮን ዶላር የማህበረሰባዊ አገልግሎት የወጭ እቅዳቸውን አስመልከቶ የዴሞክቲክ ፓርቲ አባላት እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ሆነዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በዚህ ሳምንት በሁለቱ ግዙፍ የወጭ እቅዶቻቸው ላይ በሁለት የተከፈሉ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባሎቻቸውን ወደ አንድነት የማምጣት ጫና አለባቸው፡፡

እንዲህ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ

“ይህን ነገር ተግባራዊ እንደምናደርገው እንገራችኋለሁ፡፡ መቸም ይሁን መች ግድ የለም፡፡ በስድስት ደቂቃ ይሁን በስድት ቀን ይሁን ስድስት ሳምንት ይህን ነገር እናደርገዋለን!”

ለመንገዶች ለድልዮችን አውራ ጎዳናዎች የሚውል ከሁለቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ ያገኘው የ1.2 ትሪሊዮን ዶላር የመሰረተ ልማት እቅድ የህግ መወሰኛውን ምክር ቤት አልፏል፡፡

በተወካዮቹ ምክር ቤት ያሉት ተራማጆቹ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ግን ፓርቲያቸውየማህበራዊ፣ የአካባቢ የትምህርና የህጻናት እንክብካቤ ጉዳይን በሚያጠቃልለው የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር የማህበራዊ በጀት ላይ እስኪስማማ ድረስ እንደማያጸድቁት አስታውቀዋል፡፡

የተወካዮቹ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፕሎሲ፣ ምክር ቤቱ በመሠረተ ልማቱ እቅድ ላይ ድምጽ የሚሰጥበትን ቀን በማስተላለፋቸው ውሳኔ፣ በመካከል ላይ ያሉ አንዳንድ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላትን አስቆጥቷል፡፡

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑት የአሪዞና ዴሞክራት ሴነተር ኪርስተን ሳይነማ ትልቁን የመሠረተ ልማት እቅድ መያዣ በማድረግና ማዘገየት “ይቅር የማይባል መሰናክል ነው ብለዋል፡፡

ሪፐብሊካኖችም ግዙፉን የወጭ እቅድ ተቃውመዋል፡፡ የዋዮሚንግ ሪፐብሊካን ሴነተር በፎክስ ኒውስ ሰንዴይ በተሰኘው የፎክስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ “ይህ ልጓም የሌለው ግዙፍ የመንግሥት ሶሾሊዝም እቅድ ነው” ብለዋል፡፤

XS
SM
MD
LG