በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለባይደን በዓለ ሲመት ተዘጋጅታለች


አሜሪካ ለባይደን በዓለ ሲመት ተዘጋጅታለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

አሜሪካ ለባይደን በዓለ ሲመት ተዘጋጅታለች

ከነገ በስቲያ ረቡዕ፣ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴት ምክር ቤት ህንጻ ደጃፍ ላይ፣ 46ኛ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፡፡

የፕሬዚዳንታዊውን የምርጫ ውጤት የሚቃወሙ የአገር ውስጥ ጽንፈኛ ቡድኖችም በድጋሚ ሊያደርጉት ይችላሉ የተባለውን ሁከት ለመከላከል በአገሪቱ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ መኖሩም ተመልከቷል፡፡

በዚህ ሳምንት የሚደረገው የጆ ባይደን 46ኛውን ፕሬዚዳንታዊ በዓለ ሲመት በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ፣ የታጠቁ ዘቦች ዝግጁ ሆነዋል፡፡

ቀድሞውኑም በኮቭድ 19 ሳቢያ እና እንዲሁም ባለፈው የዩናይትድ ስቴት ምክር ቤት ህንጻ ላይ በተደረገው አመጽ የተነሳ በብዙ ነገሮቹ የተገደበ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የጆ ባይደን አስተዳደር ቡድን አባላት ግን፣ ሥነ ሥርዓቱ፣ የአሜሪካ ዴሞክራሲ የማይበገር መሆኑን ለመላው አሜሪካውያንና የዓለም ማህበረሰብ ግልጽ የምናደርግበት ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዋይት ሀውስ ኮሙዩኒኬሽን ድሬክተር ኬት በዲንግፊልድ እንዲህ ይላሉ

“ተመራጩ ጆ ባይደን፣ እኤአ ጥር 20 ቀትር ላይ፣ እጃቸውን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ጭነው ለማየት፣ እጅግ በጣም ጓጉተናል፡፡”

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ጆ ባይደን ቃለ መሀላቸውን በሚፈጽሙበት ስነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት አላቀዱም፡፡ አለመገኛታቸውም በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል፡፡

ይልቁንም፣ ፕሬዚዳን ትራምፕ የግላቸውን የስንብት ፕሮግራም ለማድረግ ያቀዱት ሜሪላንድ በሚገኘው የአንድሩ የጦር ሠፈር ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ “ኤር ፎርስ ዋን” በተባለው ልዩ ፕሬዚዳንታዊ አውሮፕርላን፣ ወደ ፓልም ቢች ፍሎሪዳ ይበራሉ፡፡

ፒው የጥናትና ምርምር ማዕከል ባሰባሰበው የህዝብ አስተያየት፣ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ስራ አፈጻጸማቸውን አስመልክቶ ከሥልጣናቸው ሲሰናበቱ ያገኙት፣ የህዝብ አስተያየት ድምጽ 29 ከመቶ ነው፡፡ ይህም በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ከነበረው ሁሉ ዝቅተኛው ነው፡፡

በሌላም በኩል አሜሪካ በሚገኙ ክፍለ ግዛቶች በሚገኙ፣ የምክር ቤት ህንጻዎችም ላይ ተመሳሳይ የተቃውሞ አመጾች ይካሄዳሉ በሚል፣ ጥበቃዎች መጠናከራቸው ተነግሯል፡፡ ለምሳሌ በዋሽንግተን ክፍለ ግዛት ኦሎምፒያ ከተማ የሚገኘው ምክር ቤት ህንጻ፣ በትላልቅ መከለያዎች ታጥሯል፡፡

በዚህች ከተማ ነዋሪ የሆኑት ጆ ስለሁኔታ እንዲህ ይላሉ

“መቸስ ምን ይደረጋል፣ አሜሪካዊ ማለት፣ ምን ማለት እንደሆነ እወቀቱ የሌላቸው ሰዎች፣ ዴሞክራሲያችን ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ ለማገድ ሲባል፣ በዚህ ሰዓት፣ እነዚህን አጥሮች ማኖራችን እጅግ በጣም ያሳዘነኝ ነገር ነው፡፡”

ጆን ሄሴ፣ የተባሉት ሌላው የኦሎምፒያ ነዋሪ ደግሞ የትራምፕ ደጋፊ ሲሆኑ የሚከተለውን ብለዋል፤

“ይህ አጥርና የመሳሰሉት ነገሮች እንደኔ ዓይነት ሰዎችን ለመቃረን የተደረጉ ናቸው፣ ይህ የሚያሳየው መንግሥት በአብዛኛው አሜሪካውያን ዘንድ ምርጫው ህጋዊ ነው ተብሎ የማይታመን መሆኑን ማወቁ ነው፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከአብዛኛው አሜሪካዊውያን ፍላጎት ውጭ የተደረገውን ምርጫ ለመከላከል ነው፡፡ የተሰረቀውን ምርጫ ለመከላከል ሲሉ አጥሮችን እያጠሩ የታጠቁ ጠባቂዎችን እያመጡ ነው፡፡”

በበዓለ ሲመታቸው ወቅት፣ ለተከፋፈለችው አሜሪካ ንግግራቸውን የሚያሰሙት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ አንድነት ላይ ያተኮረ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

የባይደን ዋይት ሀውስ የኮሙኒኬሽን ድሬክተር የሆኑት ኬት በድንፊልድ እንዲህ ይላሉ፣

“ይህ አጋጣሚ፣ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሁኔታዎችን በመቀየር፣ የተከፋፈለችውን አገርና ላለፉት አራት ዓመት የተረጨውን ጥላቻን ወደ መልካምና በጎ ነገር ይቀይራሉ፡፡ አገሪቱን ብሩህ ተስፋ ወደ ተሰነቀበት ራዕይ መርተው፣ ሁላችንንም በአንድነት መስራት እንድንችል የወደፊቱን መንገድ ያመላክቱናል ብዬ አስባለሁ፡፡”

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ባለመረጋጋት መካከል አዲስ መሪ ለመቀበል ፕሬዚዳንታዊ በዓለ ሲመት የምታከናውን አገር፣ ለአሜሪካና ለዓለም የተለየ መልእክት ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ ትመስላለች፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሸል ኩዪን ያጠናቀረችው ዘገባ ነው።

XS
SM
MD
LG