የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን እና 130 ተሸከርካሪዎች ደግሞ በጉዞ ላይ መሆናቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።
ለእርዳታ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር መሻሻሎች መኖራቸውንም በቅርቡ ያስታወሱት የዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር፣ ሆኖም በየሳምንቱ በ100ዎች የሚቆጠሩ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡
የረድኤት ድርጅቶች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ከፍተኛ ረሃብ በተጠጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ወደ ሚሉት ትግራይ ክልል የሚገባው የዕርዳታ መጠን ታዲያ አሁንም ድረስ አነስተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ለዚህም በፌዴራሉ መንግሥትና በህወሓት መካከል ያለው መወነጃጀል እንደቀጠለ ነው፡፡
/በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/