በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ድርጅት 40 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በምግብ እጠረት እየተሰቃየ መሆኑን ገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ በትግራይ ጦርነት ለተጎዱ የምግብ እቃዎችን የጫኑ ኮንቮይ የዓለም የምግብ ፕሮግራም መኪናዎች በማይ ፀብሪ ከተማ፣ እአአ ሰኔ 26 ቀን 2021
ፎቶ ፋይል፦ በትግራይ ጦርነት ለተጎዱ የምግብ እቃዎችን የጫኑ ኮንቮይ የዓለም የምግብ ፕሮግራም መኪናዎች በማይ ፀብሪ ከተማ፣ እአአ ሰኔ 26 ቀን 2021

የዓለም ምግብ ድርጅት ዛሬ ባወጣው የምግብ ደህንነት ግምገማ መረጃ በትግራይ ወደ 40 ከመቶ የሚጠጋው ህዝብ 15 ወራት ከዘለቀው ግጭት በኋላ በትልቅ የምግብ እጥረት እየተሰቃየ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በግጭቱ በተጎዱ ሦስቱ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልሎችም 9 ሚሊዮን የሚጠጋ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን ገልጾ ይህ ከእከሰዛሬው ትልቁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እድሜያቸው 5 ዓመትና ከዚያ በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 13 ከመቶ የሚሆኑት እንዲሁም ሁሉም ነፍሰ ጡር ሴቶችና የሚያጠቡ ሴቶች የተመጣጠነ ምግብ እንደማያገኙም ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ይህ ጤነኛ ያልሆነ እርግዝና እንዲሁም ከክብደታቸው በታች ሆኖ መወለድና የወሊድ ወቅት ሞትን የሚያስከትል መሆኑም በተደረገው ጥናታዊ ቅኝት የተመለከተ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የዓለም ምግብ ድርጅት ሊቀመንበር ዳይሬክተር ማይክ ደንፎርድ ይህ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚሰጠው የሰብ አዊ ድጋፍ ከፍ ማለት ያለበት መሆኑና ተረጅዎቹም አሁኑኑ የሚፈልጉት መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG