በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ከዩክሬን ግዛት ሃያ ከመቶ የሚሆነውን ይዛለች ሲሉ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ተናገሩ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ሃያ ከመቶውን የሀገራችንን መሬት ተቆጣጥራለች ሲሉ ተናገሩ፡፡ ውጊያው የሚካሄድባቸው ግንባሮች ርዝማኔ ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ይበልጣል ብለዋል፡፡ ሀገራቸው ስለተሰጣት እርዳታ ታመሰግናለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ የጦር መሳሪያ እርዳታው እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የዩክሬኑ ጦርነት አራተኛ ወሩን የያዘ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ሰባት መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት፣

"በይበልጥ የተራቀቀ ሮኬት እና ሌሎችም የጦር መሳሪያዎች ለዩክሬን እንደምትልክ ትናንት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል፡፡ዩክሬን ሮኬቶቹን ወደሩሲያ ግዛት ውስጥ እንደማትተኩስ ቃል መግባቷን የዋይት ሀውስ ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡ ትናንት በዋሽንግተን የኔቶ ዋና ጸሀፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ጋር ሆነው በሰጡት ቃል “ይህ ጦርነት እንዴት አና መቼ እንደሚያበቃ አይታወቅም ሆኖም የሰላም ድርድር ደረጃ ላይ ሲደረስ ዩክሬን ጠንካራ ቁመና ይዛ እንድትገኝ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

ብሊንከን፣

“ውጊያውን የማብረዱም ሆነ የማቆሙ አቅም ያለው በሩሲያ እጅ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን ማክሰኞ እለት በኒው ዮርክ ታይምስ የአስተያየት አምድ ላይ ባወጡት ጽሁፍ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ከሚስተር ፑቲን ጋር የማንስማማ መሆናችን እና አድራጎታቸው የሚያስቆጣ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች አጋሮቿ ፑቲን ከሥልጣን እንዲወገዱ ለማድረግ አይሞክሩም ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮችዋ ላይ ጥቃት ካልደረሰ በስተቀር ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች በቀጥታ ግጭቱ ውስጥ አይገቡም ብለዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ዩክሬይን ሮኬት ወንጫፊ መሳሪያ ካገኘች ጦርነቱ አንዲስፋፋ ያደርጋል በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG