በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩንጋንዳ ወታደሮችዋን በምስራቅ ኮንጎ ግዛት አሰማራች


የዩናጋዳ በኮንጎ ዲሞክትራቲክ ሪፐብሊክ ያሉትና የተባበሩት ዴሞክራሲ ኃይሎች ወይም ኤዲፍ የሚባሉትን አማጽያን ለመዋጋት ከኪንሻሳ ጋር ባደረገችው የጋራ ትብብር ወታደሮችዋን ወደዚያው ማሰማራቷን የዓይን እማኞች ተናገሩ፡፡

የዩጋንዳ ወታደሮች ባለፈው ማክሰኞ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ድንበር አልፈው ወደ ውስጥ መዝለቅ የጀመሩት ሠራዊቱ በአማጽያኑ ላይ የአየርና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ መሆኑን የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ኤዲኤፍ የተባሉት አማጽያን በኮንጎ ምስራቃዊ ግዛትና በዩናጋንዳ በደረሱ ተከታታይ የቦምብ ጥቃቶችና የጅምላ ፍጅቶች ኃላፊነቱን የወሰደው የእስላማዊ መንግሥት አራማጅ ቡድን ተባባሪዎች መሆናቸውም የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካቶሊክ ቤተከርስቲያን፣ አማጽያኑ እኤአ ከ2013 ጀምሮ ወደ 6ሺ ሰዎችን መግደላቸውን አስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG