በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩጋንዳ ተማሪዎችን በሽብር ያጠቃው ቡድን በአይሲስ እንደሚደገፍ ተገለጸ


ባለፈው ዓርብ፣ በዩጋንዳ፣ በአንድ ት/ቤት ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ የሞቱት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዐት እየተከናወነ ነው።
ባለፈው ዓርብ፣ በዩጋንዳ፣ በአንድ ት/ቤት ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ የሞቱት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዐት እየተከናወነ ነው።

ባለፈው ዓርብ፣ በዩጋንዳ፣ በአንድ ት/ቤት ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ የሞቱት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዐት እየተከናወነ ነው። ጥቃቱን የፈጸመው ኤ.ዲ.ኤፍ. በመባል የሚታወቀው፣ የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቡድን፣ በጽንፈኛው እስላማዊ መንግሥት(ISIS) በገንዘብ እንደሚደገፍ፣ የተመድ ባለሞያዎች ጥናት አመለከተ።

ዩጋንዳን ከኮንጎ በሚያዋስነው አካባቢ በሚገኘው ት/ቤት ላይ በደረሰው የሽብር ጥቃት፣ ከሞቱት 42 ሰዎች ውስጥ 38ቱ ተማሪዎች ሲኾኑ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ፣ የት/ቤቱ ዘብ እና ሌሎቹ ሦስቱ ሲቪሎች እንደኾኑ ታውቋል።

አንዳንዶቹ ተማሪዎች፣ መልካቸው በማይለይበት ደረጃ እንደተቃጠሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ በስለት እና በጥይት እንደተገደሉ ተገልጿል። ቢያንስ ስድስት ተማሪዎችም፣ ተጠልፈው ወደ ኮንጎ ሳይወሰዱ እንዳልቀረ፣ የዩጋንዳ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ጥቃቱን ፈጻሚው ኤ.ዲ.ኤፍ.፣ በምሥራቅ ኮንጎ፣ በሺሕ በሚቆጠሩ ሲቪሎች ግድያም ተጠያቂ እንደሆነ፣ የተመድ ባለሞያዎች ጥናት ጠቁሟል።

ቡድኑ፣ እ.አ.አ ከ2019 ጀምሮ፣ በአይሲስ የገንዘብ ድጋፍ ሲደረግለት እንደቆየና ገንዘቡ፣ በግለሰቦች አማካይነት ከሶማሊያ ተነሥቶ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ በኩል እንደሚሸጋገር፣ በያዝነው ሳምንት ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቀው የተመድ ጥናት አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG