በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኡጋንዳ የኢቦላ ተጋላጮች ቁጥር ጨምሯል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ውስጥ ካለፈው ዓርብ ወዲህ ለኢቦላ ቫይረስ የተጋለጡ 11 ሰዎች መገኘታቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ራቅ ባሉት የምስራቅ አፍሪካዪቱ አገር አካባቢዎች ወረርሺኙ ከአንድ ወር በላይ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በዋና ከተማዋ ካምፓላ አካባቢ ባላፈው ዓርብ ለቫይረሱ ከተጋለጡ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ትናንት እሁድ ደግሞ ሌሎች 9 የሚሆኑ ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስትሩ ጄን ሩት አሴንግ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛው ባለሥልጣን ባላፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ በኡጋንዳ ወረርሽኙ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋና ለጤና ሠራተኞች አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

እአአ ካለፈው መስከረም 20 ወዲህ 75 የኢቦላ ተጋላጮች እንደነበሩና ከመካከላቸው 28ቱ መሞታቸውን የኡጋንዳ ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል ሲል አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG